This page contains information about the Department of Employment Services for Amharic speakers.
የወኪል ስም: የዲ.ሲ የቅጥር አገልግሎቶች መምሪያ (D.C. Department of Employment Services)
ተልዕኮ:
የቅጥር አገልግሎቶች መምሪያ ተወዳዳሪ የሰው ሃይል፣ መሉ ቅጥር፣ የእድሜ ልክ ትምህርት፣ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና ከፍ ያለ አኗኗር ለአውራጃው ነዋሪዎች በሙሉ ለማረጋገጥ የተሟላ የቅጥር አገልግሎቶችን ያቀርባል፡፡
ዋና ፕሮግራሞች/የክፍል መግለጫ፡
የሰው ኃይል መስፈርቶች( Labor Standards )
የሰው ሃይል መስፈርቶች የኮሎምቢያ አውራጃ የሰው ኃይል ህግጋትን ያሰታደደርል እንዲሁም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ቢሮው የክፍያ ቅሬታዎችን ይመረምራል፣ በስራ ቦታ የሰራተኞችን እና የአሰሪዎችን ደህንነት/ጤና ይገመግማል፣ እንዲሁም በስራ ላይ አደጋ የደረሰባቸውን የግል ተቀጣሪ ሰራቶች ካሳ/ህክምና ክፍያ ጥያቄዎችን ይዳኛል፡፡ በተጨማሪም የሰራተኞች የካሳ ጥቅም ጥቅም ጥያቄ ላይ የሚነሱ አለመግባባቶችን የመፍታት ሂደቱን ለማገዝ ቢሮው አሰተዳደራዊ እና መካከለኛ የፍርድ ስርአቶችን ያቀርባል፡፡ የሰው ኃይል መስፈርቶች/የሰራተኛ ጥበቃ የሚመራው እና የሚተዳደረው በሰው ኃይል መስፈርቶች ጽህፈት ቤት በኩል ነው፡፡
የወጣቶች አገልግሎቶች (Youth Services)
የወጣቶች ፕሮግራሞች ጽህፈት (ወ.ፕ.ጽ) ቤት በአውራጃው ለሚገኙ ዕድሜያቸው 14-24 ለሆኑ ወጣቶች የሰው ኃይል እድገት ፕሮግራሞችን ያደረጃል እንዲሁም ያስተዳድራል፡፡ ወ.ፕ.ጽ በስራ ቦታ ስኬትን ለማስመዝገብ አሰፈላጊ የሆኑትን የሰራ ባህል እና ክህሎቶችን እድገት ለማመቻቸት ሙያዊ ልምምዶችን፣ የስራ ልምድ፣ የቀልም ትምህርት፣ እና የህይወት ክህሎቶች ልምምዶችን ያቀርባል፡፡
የስራ አጥነት ካሳ (Unemployment Compensation)
የስራ አጥ መድህን የኮሎምቢያ አወራጃ የብቃት መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ግለሰቦች ለአጭር ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ/ዷ የመድህን ጥቅማ ጥቅሞችን የሚወስድ/የምትወስድ በአውራጃው የወጡትን ደምቦች እንደሚከተል/እንደምትከተል የማረጋገጥ ህጋዊ ሃላፊነት አለበት/አለባት፡፡ የስራ አጥ መድህን ፕሮግራም ክፍያ ፋይናንስ የሚሸፈነው አሰሪዎች ከእያንዳንዱ ሰራተኛ የጉልበት ክፍያ ላይ በአመት በመሰበሰብ ከሚከፍሉት የግዛት እና የፌደራል ታክሶች ላይ ነው፡፡
የሰው ኃይል እድገት ጽህፈት ቤት (Workforce Development Bureau)
የሰው ኃይል እድገት ጽህፈት ቤት ለሚከተሉት ፕሮግራሞች አሰተዳደራዊ እይታ፣ እቅድ፣ እና የፖሊሲ እድገትን ያቀርባል፡ የአሜሪካ የሰራ ማዕከላት (American Job Centers (AJCs)፣ የንግድ አገልግለቶች ቡድን (Business Services Group)፣ ፕሮጀክት የማብቃት/የሽግግር የቅጥር ፕሮግም (Empowerment (PE)/Transitional Employment Program (TEP))፣ በስራ ላይ ልምምድ መረጃ እና ልምምድ (Apprenticeship Information and Training)፣ የሰው ኃይል ገበያ መረጃ (Labor Market Information (LMI))፣ እና ልዩ የቅጥር ፕሮግራሞች (Special Employment Programs) ለምሳሌ የአዛውንቶች እርዳታዎች እና የጦር ሜዳ ተመላሾች ፕሮግራሞች፡፡
አገልግሎቶች:
የአሜሪካ የስራ ማዕከል( American Job Center)
የአሜሪካ የስራ ማዕከል ቀድሞ የዲሲ ስራዎች! አንዴ የሚቆሙበት ማዕከል፣ ለስራ ፈላጊዎች፣ ተማሪዎች፣ ንግዶች፣ እና በለሞያዎች አንድ አመቺ በሆነ ቦታ ከቅጥር ተያያዥነት ያለቸውን አገልግሎቶች እና መሳሪያዎች ያቀርባል፡፡ በአውራጃው የአሜሪካ የስራ ማዕከል በኩል ነዋሪዎች ከዚህ የሚከተሉትን ሃብቶች መጠቀም ይችላሉ፡ ለምሳሌ የምክር፣ የሞያ እቅድ፣ የስራና ትምህርት ልምድ አዘገጃጀት ድጋፍ፣ ቀጥታ የስራ ቅጥር፣ የክፍል ውስጥ እና የስራ ላይ ልምምድ፣ ሰለብሄራዊ እና አለምአቀፍ የሰው ኃይል ገበያ እና ሌሎችንም፡፡ የቅጥር አገልግሎቶች ክፍል፣ ከአውራጃው መንግስት በሚያገኘው ሃብት በመታገዝ በስትራቴጂ አቅጣጫቸው ተለይቶ በአወራጃው ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆኑ ተደርገው የተቀመጡት ማእከላት ያንቀሳቅሳል፡፡
የስራ ላይ ትምህርት (Apprenticeships)
የስራ ላይ ትመህርት ሁለቱንም ማለትም የስራ ላይ ለምምድን ከክፍል ውስጥ ትምህርት ጋር የሚያዋህድ ነው፣ ከፍተኛ ክህሎት ለሚጠይቁ ስራዎች ተግባራዊውን እና ቲዎሪቲካል አቅጣጫውን የሚያስጨብታቸው ነው፡፡ የስራ ላይ ትምህርቶች ስፖንሰር የሚደረጉት በቀጣሪዎች፣ የሰው ሃይል ቡድኖች እና የቀጣሪዎች ማህበራት ነው፡፡ የቅጥር አገልግሎቶች መመሪያ (ቅ.አ.መ.) (Department of Employment Services (DOES)) አካል የሆነው የስራ ላይ ትምህርት መረጃ እና ልምምድ (ስ.ት.መ.ል) (Apprenticeship Information and Training (OAIT)) ጽህፈት ቤት፣ የሰራ ላይ ትምህርት ተማሪዎችን እና የስራ ላይ ትመህርት ፕሮግራሞችን ይመዘግባል፡፡ ስ.ት.መ.ል. የተማሪዎችን ደህንነት ይጠብቃል፣ የፕሮግሞቹን ጥራት ያረጋግጣል፣ ለትምህርት እኩል እድል እንዳለ ያረጋግጣል፣ ለስፖንስሮች፣ ቀጣሪዎች፣ እና አለማማጆች የተቀናጀ የቅጥር እና የልምምድ መረጃ ያቀርባል፡፡
እንዲሁም OAIT የኮሎምቢያ አውራጃን የስራ ላይ ትምህርት ምክር ቤትን (District of Columbia Apprenticeship Council) ሰራተኞች ያደራጃል፡፡ የስራ ላይ ትምህርት አመልካቾች ቢያንስ 16 ዓመት ሊሆናቸው የሚገባ ሲሆን የስፓንሰሮችን መስፈርቶችንም ማሟላት አለባቸው፡፡ በአጠቃላይ፣ አመልካቾች የስራ ሃላፊነቱን ውስጠሚስጥር ተገንዝበው ስራውን በሚገባ የማከናወን ብሎም ተዛማጅ መመሪያን የመፈፀን ችሎታ፣ ክህሎት እና ትምህርት እንዳላቸው ለስፓንሰሮች ማሳየት አለባቸው፡፡ እጩ ተቀጣሪዎች ከOAIT ተወካዮች በመሆን የስራ-ላይ-ስልጠና ዕቅዶችን እና ተዛማጅ የክፍል ውስጥ ትምህርት፣ እንዲሁም ስራ የማከናወን ሂደቶችን በመስራት ላይ ናቸው፡፡
የካሳ ግምገማ ቦርድ (Compensation Review Board)
የካሳ ግምገማ ቦርድ፣ እንዳንድ ጊዜ CRB ተብሎ የሚጠራው፣ በፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚል ወኪል የሚያገለግል ሲሆን የቅጥር አገልግሎቶች መምሪያ የሰራተኞች ካሳ ቢሮ እና የይግባኝ ሰሚ እና ድርድር ቢሮ (Department of Employment Services Office of Workers Compensation and Office of Hearings and Adjudication) የሰራተኞች ካሳ ጥቅማ ጥቅም ውሳኔዎች አግባብነት የመገምገም ሃላፊነት አለበት፡፡ የCRB ውሳኔ ምንአልባትም ለዲ.ሲ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የይግባኝ ጥያቄ በማስገባት ሊፈተን ይችላል፡፡
የስራ ባንክ አገልግሎቶች (Job Bank Services)
የስራ ባንክ የዲሲ ኔትወርክ ስርዓት አካል ነው፣ በኮምፒውተር የተመዘገበ ብሔራዊ የሰራተኛ ልውውጥ ኔትወርክ ነው፡፡ ስርዓቱ የተነደፈው ቀጣሪዎችን ከስራ ፈላጊዎች ጋር ለማዛመድ ነው፡፡ ማንኛውም ቀጣሪ፣ ሁለቱም አካባቢያዊም ሆነ ብሔራዊ፣ የስራ ትዕዛዛትን ለመስጠት እና አመልካቾችን በቀጣሪው በተቀመጠ የችሎታ መስፈርት ወይም የስራ ድርሻ መሰረት ለመቅጠር ይረዳ ዘንድ የተነደፈ ስርዓት ነው፡፡ የስራ ባንክ ክፍል ክፍት የስራ ቦታን ለማውጣት የሚጠይቁ ቀጣሪዎችን በማማከር፣ ስልጠና በመስጠት እና የቴክኒክ እገዛን በማበርከት፣ ብቁ የሆኑ ተቀጣሪዎችን በመለየት፣ አሁን ያለውን እና አካባቢያዊ የስራ ገበያ ዳታን በማጥናት ብሎም ደግሞ የቅጥር ክፍያን በመክፈል አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ፕሮግራሙ ዓመቱን ሙሉ የሚሰጥ ነው፡፡
የይግባኝ ሰሚ እና ድርድር ቢሮ (Office of Hearings and Adjudication)
የይግባኝ ሰሚ እና ድርድር ቢሮ ለግሉ ዘርፍ ሰራተኞች እና በኮሎምቢያ አውራጃ አስተዳደር ውስጥ ላሉ በስራ ላይ ለተጎዱ ተቀጣሪዎች የአካል ጉዳተኝነት ጥቅማጥቅሞችን ለመወሰን አካሄዱን የተከተለ አስተዳደራዊ የይግባኝ ጥያቄዎችን ያስተናግል፡፡ የአስተዳደር ህግ ዳኞች ህጉን መሰረት በማድረግ ይግባኙን ከሰሙ በኋላ በጉዳዩ ላይ ውሳኔን ይሰጣሉ፡፡ የኮሎምቢያ አውራጃ ሰራተኞች ካሳ አዋጅ 1979፣ እንደተሻሻለው፣ የግሉ ዘርፍ ሰራተኞች ለአካል ጉዳተኞች ጥቅማ ጥቅም ብቁ ያደርጋቸዋል፡፡ የኮሎምቢያ አውራጃ አስተዳደር ሁሉን አቀፍ የሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ 1978፣ እንደተሻሻለው፣ የኮሎምቢያ አውራጃ አስተዳደር ሰራተኞችም ለአካል ጉዳተኝነት ጥቅማጥቅሞች ብቁ እንደሆኑ ያዛል፡፡
የስራ ላይ ደህንነት እና ጤና ቢሮ (Office of Occupational Safety and Health)
የስራ ላይ ደህንነት እና ጤና ቢሮ (Office of Occupational Safety and Health (OSH)) በኮሎምቢያ አውራጃ ውስጥ ላሉ የግሉ ዘርፍ ሰራተኞች ነፃ የምክር አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ OSH ቀጣሪዎች የደህንነት እና የጤና አስተዳደር ፕሮግራምን እንዲያቋቁሙ እና አገልግሎቱንም እንዲሰጡ ያግዛል፣ ይህም በተቻለ መጠን፣ ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር ነው፡፡ ቀጣሪዎች በስራ ቦታቸው ላይ አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለይተው ማወቅ ይችላሉ፣ ስልጠናን በመውሰድ የስራ ቦታቸውን ደህንነት እና የጤና ፕሮግራም ማሻሻል ይችላሉ፡፡ ምንም ማጣቀሻዎች አይሰጡም እንዲሁም ውጤቶቹ ሚስጥራዊ ናቸው፡፡ የእርስዎ ግዴታ የሚሆነው ከባድ የሆኑ የስራ ላይ የደህንነት እና ጤናን የሚያውኩ አደገኛ ሁኔታዎችን ለማረም ቁርጠኛ መሆን ብቻ ነው፣ በትክክለኛው ጊዜ ከእርስዎ የሚጠበቀውን ሃላፊነት የመወጣት ቁርጠኝነት፡፡
የደምወዝ ሰዓት ቢሮ (Office of Wage Hour)
የደምወዝ ሰዓት ቢሮ የኮሎምቢያ አውራጃን የደምወዝ ህግጋት ያስተዳድራል እንዲሁም በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ ዝቅተኛ የደምወዝ ክፍያ፣ በሳምንት ከአርባ ሰዓት በላይ ከተሰራ የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ ለአውራጃ አስተዳደር ኮንትራክተሮች የሚከፈል የደምወዝ ክፍያ፣ በህመም ወይም ከቤት ውስጥ ጥቃት ጋር ተዛማጅነት ባለቸው ነገሮች ምክንያት በስራ ገበታቸው ላይ ላልተገኙ የሚከፈል ክፍያ፣ የሚከፈለው ደምወዝ ወቅቱን ጠብቆ ስለመከፈሉ የመሳሰሉትን ይከታተላል፡፡ የደምወዝ ሰዓት ቢሮ ላላተከፈሉ እና ግጭት ላለባቸው የደምወዝ ክፍያዎች የማደራደር አገልግሎትን ይሰጣል፡፡
የሰራተኞች ካሳ ቢሮ (Office of Workers’ Compensation)
የሰራተኞች ካሳ ፕሮግራም በኮሎምቢያ አውራጃ ውስጥ ያሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የግሉ ዘርፍ ተቀጣሪዎች ጥያቄ ሂደትን ይመለከታል እንዲሁም ክፍያውን እና ጥቅማ ጥቅሙን ይቆጣጠራል፡፡ በጥያቄ አቅራቢዎች እና በቀጣሪዎች (ወይም የእነርሱ ኢንሹራንስ አቅራቢ) መካከል የሚኖር ግጭት እንዲደራደሩ ይደረጋል፣ እና ቀጣሪዎች በኢንሹራንስ ሽፋኑን መስፈርት መከተላቸውን ለማረጋገጥ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ ፕሮግራሙ ልዩ/ሁለተኛ የጉዳት ገንዘብን ያስተዳድራል፣ ይህም ኢንሹራንስ ለሌላቸው ቀጣሪዎች ወይም ጉዳቱ ከዚህ ቀደም ከነበረ የአካል ጉዳት ጋር ተጣምሮ ዘላቂ የሆነ እና ከባድ የአካል ጉዳትን የሚያስከትል ሲሆን ነው፡፡ እንዲሁም፣ ፕሮግራሙ አጠቃላይ ክፍያዎችን ያጸድቃል፣ ሽፋን ለሌላቸው ህጉ ላይ መሰረት በማድረግ የመቀጫ ክፍያዎችን እና ቅጣቶችን ይገመግማል፣ እና ሞያቂ ማገገሚያ ስፍራዎችን ይቆጣጠራል፡፡
የፕሮጀክት ማብቃት ፕሮግራም
የፕሮጀክት ማብቃት ለአውራጃው ነዋሪዎች የስራ ዝግጁነት ስልጠናን እና የማካካሻ ቅጥርን የሚሰጥ የሽግግር የቅጥር ጊዜ ነው፡፡ ተሳታፊዎች ተከታታይ በሆነ የሶስት ሳምንት ስልጠናን ይሳተፋሉ፣ ከዚያም ለስድስት ወራት የማካካሻ የቅጥር ሁኔታ ላይ ይመደባሉ፣ እንዲህ ባለው ሁኔታ ሁሉም ቋሚ ለሆነ እና ማካካሻ ለሌለው የቅጥር እድል ለማግኘት ይሰራሉ፡፡
ስራ የሌላቸው ኢንሹራንስ ታክስ (Unemployment Insurance Tax)
ስራ የሌላቸው ኢንሹራንስ የፌደራል መንግስት ፕሮግራም ሲሆን ከእነርሱ ጥፋት ውጭ ስራ ለሌላቸው እና ስራን መስራት የሚችሉ ብሎም ለስራ ዝግጁ ለሆኑ ሰራተኞች ጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅምን የሚሰጥ ፕሮግራም ነው፡፡ ስራ ለሌላቸው ሰራተኞች የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞች የስራ አጥነትን ችግሮች ይቀንሳል፣ ያልተቀጠሩ ሰዎች የመግዛት አቅማቸው ባለበት እንዲቆይ (እንዲረጋጋ) ይረዳል፣ ስለሆነም የሃገር ውስጥ ኢኮኖሚን ያግዛል፣ እንዲሁም የስራ ሃይልን ያረጋጋል ስለዚህም ቀጣሪዎች ዳግም ለመቅጠር በሚፈልጉ ጊዜ የሃገር ውስጥ ሰራተኞች ለቅጥር እንዲገኙ ለማደረግ ያግዛል፡፡
ፈጣን ምላሽ (Rapid Response)
የፈጣን ምላሽ (Rapid Response (RR)) አገልግሎቶች የሚከናወኑት በሃገሪቱ እና በአካባቢያዊ የስራ ሃይል እድገት ወኪሎች እና በሃገር ውስጥ ካሉ የአሜሪካ የስራ ማዕከላት (American Job Centers) ጋር በጋራ በመስራት ነው፡፡የRR ቡድን በስራ ቅነሳ እና የድርጅቶች መዘጋትን በመከተል ለሚመጣ ስራ አጥነት አገልግሎቶችን በማስተባበር እና ለኩባንያዎች እንዲሁም በመዘጋቱ እክል ለሚገጥማቸው ሰራተኞቻቸው አስቸኳይ ድጋፍን በመስጠት ፈጣን የሆነ ምላሽን በተግባር ያውላል፡፡ ቡድኑ ከቀጣሪዎች እና ከተቀጣሪ ተወካዮች ጋር በመሆን የህዝብ እና የግለሰብ ሃብቶችን በፍጥነት ለማሳደግ፣ እና በስራ ማጣት ምክንያት የሚፈጠሩ ብጥብጦችን ለመቀነስ ይሰራል፡፡ RR እክል በለገጠመው ኩባንያ ብጁ የሆኑ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ የስራ ፈረቃዎችን ያስተባብራል፣ እና ለኩባንያዎች ብሎም ለሰራተኞች ከስራ ማጣት ጋር በተያያዘ በሽግግር ወቅት እገዛን ያደርጋል፡፡ ይህ ፕሮግራም አመቱን በሙሉ የሚሰጥ ነው፡፡
የአረጋውያን ማህበረሰብ አገልግሎት የቅጥር ፕሮግራም (Senior Community Service Employment Program)
የአውራጃው የአረጋውያን ማህበረሰብ አገልግሎት የቅጥር ፕሮግራም (Senior Community Service Employment Program(SCSEP)) እድል ላላገኙ እና ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ የአውራጃው ነዋሪዎች የማካካሻ የሞያ ስልጠናን እና የስራ ምደባ እገዛን ይሰጣል፡፡ ፕሮግራሙ ፣ ምልመላ፣ ስልጠና እና የቅጥር ስትራቴጂዎችን ያካተተ ሲሆን አረጋውያን በአደገው ኢንዱስትሪ ውስጥ በሚያስተናግዱ ኤጀንሲዎች አማካኝነት ስልጠና እና ቅጥር እንዲያገኙ ያግዛል፡፡ አስተናጋጅ ኤጀንሲዎች በቂ የሆነ የሞያ ስልጠናን እና ለቅጥር የሚያበቃ ሞያዊ እድገትን በአግባቡ መስጠት እንዲችሉ፤ በንቃት ተሳትፎ በማድረግ ተሳታፊዎች ወደ ማካካሻ የሌለው ቅጥር በሚያደርጉት ሽግግር ከቀጣሪዎች ጋር በማስተባበር ማካካሻ የሌለው ቋሚ ቅጥር የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ SCSEP የአስተናጋጅ ኤጀንሲዎችን ሃላፊነት ለማጠንከር ያልማል፡፡ እንዲሁም SCSEP ብቃት ያላቸውን፣ የሰለጠኑ እና በሳል ሰራተኞችን ለመቅጠር ፍላጎት ላላቸው ቀጣሪዎች ከስራ ጋር ተዛማጅ እገዛን የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም የSCSEP ሰልጣኞችን ለሚያስተናግዱ መንግስታዊ እና ትርፍ አልባ ኤጀንሲዎች ክፍያ የሌለው የማህበረሰብ አገልግሎት እገዛን ይሰጣል፡፡
የስራ እድል የታክስ ክሬዲት (Work Opportunity Tax Credit)
የስራ እድል የታክስ ክሬዲት (Work Opportunity Tax Credit)(WOTC)) በፌደራል የሚደገፍ ከተመረጡ ተደራሽ ቡድኖች ውስጥ አዲስ ተቀጣሪዎችን ለሚቀጥሩ የግል እና ትርፋማ ቀጣሪዎች የፌደራል ታክስ ክፍያን የሚቀንስ ፕሮግራም ነው፡፡በዚህ ተደራሽ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ስራ ለማግኘት ችግር የነበረባቸው ናቸው፡፡ ብቃት ያላቸውን አመልካቾች የቀጠሩ ቀጣሪዎች ከWOTC ፕሮግራም ከታክስ ነፃ እድልን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ የክሬዲት መጠኑ በሚከፈል ደምወዝ ፣ በተሰራበት ሰዓት፣ በአግባቡ የምስክር ወረቀት ባላቸው ተቀጣሪዎች ፐርሰንት ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም አመቱን በሙሉ ይሰጣል፡፡
የማስተርጎም አገልግሎቶች፡
የሚፈለጉ የማስተርጎም አገልግሎቶች በሚጠየቁ ጊዜ የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡ ደንበኞች ለDOES ፕሮግራም እና ዝግጅት የእኩል እድል ቢሮን (Office of Equal Opportunity) በስልክ ቁጥር (202) 671-0891 በመደወል የትርጉም አገልግሎትን መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአድራሻ መረጃ:
እባክዎን ለተጨማሪ ጥያቄዎችን በአካል በመምጣት ወይም በስልክ፣ በፋክስ አልያም በኢሜይል በሚከተለው አድራሻ ያግኙን፡
4058 Minnesota Avenue, NE
Washington, DC 20019
Phone: (202) 724-7000
Fax: (202) 673-6993
Email: [email protected]